News Amharic

የአሳታሚነትና የፐብሊሺንግ ውል ከአይቤክስ ባንድ ጋር

ሙዚቃዊ የፐብሊሺንግና የአርቲስት ውል ከአንጋፋው አይቤክስ ባንድ ጋር ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱን ጆቫኒ ሪኮና ሰላም ስዩም በአይቤክስ ባንድን በኩል የተፈራረሙ ሲሆን ይህ ስምምነት ሙዚቃዊ ቀደም ሲል የተሰሩ የአይቤክስ ስራዎችን እንዲያወጣ እንዲሁም ከባንዱ ጋር ወደ ፊት አብሮ እንዲሰራ ያስችላል፡፡

ብርትኳን መብርሀቱ ወይም ገሬዋኒ በመባል የምትታወቀው የትግርኛ ሙዚቃ ተጫዋች አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ

ሙዚቃዊ : በገሬ ቁጥር 1 እና 2 ተወዳጅነትን ያተረፈችውን የብርትኳን መብራህቱን ወይም የገሬዋኒን “ሽህ ምውላድ” የተሰኘ አዲስ የትግርኛ ነጠላ ዜማ በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናልና በሁሉም የዲጂታል መተግበሪዎች ለሙዚቃ ወዳጆች አደረሰ። በመቐለ ከተማ ተወልዳ ያደገችው ብርትኳን የሙዚቃ ጉዞ በሰርከስ ትግራይ የጀመረ ሲሆን በኦሳ ትግራይ ምግባረ ሰናይ ድርጅት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመውሰድና መድረክ ላይ በመጫወት ዳበረ። ይህም ብዙ በሮችን …

ብርትኳን መብርሀቱ ወይም ገሬዋኒ በመባል የምትታወቀው የትግርኛ ሙዚቃ ተጫዋች አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ Read More »

ሙዚቃዊ  ከትግራይ ባህል ቡድን ጋር በመሆን ከሰራው የአሸንዳ አልበም መሀል “ዕቡነይ” የተሰኘው ነጠላ ዜማ ተለቀቀ

በነሀሴ ወር ላይ በጉጉት ከሚጠበቀው አሸንዳን በዓል ምክንያት በማድረግ ሙዚቃዊ ከትግራይ ባህላዊ ቡድን ጋር በመሆን “የአሸንዳ ጨዋታዎች” የተሰኘ አልበም ያዘጋጀ ሲሆን ከአልበሙ መሀከል “ዕቡነይ” የተሰኘውን ነጠላ ዜማ ለቅምሻ ይሆን ዘንድ በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም በሁሉም የዲጂታል መተግበሪያዎች ተለቀቀ። በ1960 ዓ.ም የተመሰረተው የትግራይ ባህል ቡድን በትግራይ ክልል ትልልቅ ስራዎችን የሰራ ቡድን ሲሆን ዝነኛና ስመጥር አርቲስቶችንም አፍርቷል። …

ሙዚቃዊ  ከትግራይ ባህል ቡድን ጋር በመሆን ከሰራው የአሸንዳ አልበም መሀል “ዕቡነይ” የተሰኘው ነጠላ ዜማ ተለቀቀ Read More »

የሀብታሙ ተድላ “አወይ የኛ ነገር” የተሰኘው ነጠላ ዜማው ተለቀቀ

ከውቢቷ ጎንደር የተገኘው ሀብታሙ ተድላ “አወይ የኛ ነገር” የተሰኘውን አዲስ ነጠላ ዜማውን በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እና ዲጂታል መተግበሪያዎች አማካይነት ለሕዝብ አድርሷል። ሀብታሙ የሙዚቃ ጉዞውን የጀመረው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን ካጠናቀቀ በኋላ በፍካት ትያትርና የሙዚቃ ቡድን እንዲሁም ሰርከስ ጎንደር ሲሆን ዘግየት ብሎ ግን የመከላከያ ኦርኬስትራን በመቀላቀል፤ ፕሮፌሽናል ክህሎትን አዳብሯል::  ሀብታሙ በሙዚቃ ጉዞ ውስጥ ጉልህ ስኬቶችን ያገኘ ሲሆን …

የሀብታሙ ተድላ “አወይ የኛ ነገር” የተሰኘው ነጠላ ዜማው ተለቀቀ Read More »

እውቁ ሙዚቀኛ ኪሮስ ግርማይ ‘ናፍቆት’ የተሰኘው ነጠላ ዜማውን ለአድማጮች አደረሰ

በውቅሮ ትግራይ የተወለደው ኪሮስ ግርማይ ‘ናፍቆት’ የተሰኘው አዲሱ ነጠላ ዜማውን ለአድማጮች አድርሷል፡፡ ልጅእያለ ምንም እንኳን የሙዚቃ ፍቅሩ የቤተሰብ ድጋፍ ባያገኝም በልጅነቱ ለውዝዋዜ የነበረው ፍቅር ወደ ጥልቅ የሙዚቃ ፍቅርናሞያ ሊያድግ ችሏል፡፡ ኪሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ውቅሮ በሚገኘው በከነማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በአጋዚ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የተከታተለ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት …

እውቁ ሙዚቀኛ ኪሮስ ግርማይ ‘ናፍቆት’ የተሰኘው ነጠላ ዜማውን ለአድማጮች አደረሰ Read More »

የጆርጋ መስፍን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ ኢትዮ ጃዝ አልበም ተለቀቀ

ጆርጋ መስፍን በኢትዮ ጃዝ ዓለም እውቅ ሙዚቀኛ ሲሆን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ የተሰኘውን አልበሙን ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም በዲጂታል መተግበሪያዎች  ለአድናቂዎቹ አድርሷል፡፡ ዶ/ር ሙላቱ አስታጥቄ በሞያ ኮትኩቶ ያሳደገው የጆርጋ መስፍን አልበም በተለይም የኢትዮጵያ ጃዝ ሙዚቃ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ይዘቶች ጋር መንፈሳዊነትን በማዋሃድ ኢትዮ ጃዝን የሚያስቃኝ አልበም ነው፡፡ ጆርጋ የሙዚቃ ጉዞውን …

የጆርጋ መስፍን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ ኢትዮ ጃዝ አልበም ተለቀቀ Read More »

አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል እና የአፍሪካ ቀን ክብረ-በዓል ከግንቦት 16 – 18 በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ በጋራ ሊካሄዱ ነው

አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል በኢትዮጵያ እውቅ የሙዚቃና የሁነት ፕሮዳክሽን ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ሙዚቃዊ የሚታወቅበት  ዝግጅት ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው የሆነው ፌስቲቫል አንጋፋና አዳዲስ ሙዚቀኞችን እንዲሁም የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ አርቲስቶች የሰሯቸውን አዳዲስ ስራዎች ያቀርባል፡፡ የፌስቲቫሉ የማስጀመሪያ ስነስርዓት በ2012 ዓ.ም የተደረገ ሲሆን አላማውም የጃዝ ሙዚቃን ለአዲስ አበባ ማስተዋወቅ እና ለአለም አቀፍ የጃዝ ሙዚቀኞች የትስስር እድልና መድረክ …

አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል እና የአፍሪካ ቀን ክብረ-በዓል ከግንቦት 16 – 18 በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ በጋራ ሊካሄዱ ነው Read More »

ጎንደር ፋሲለደስ የባህል ቡድን በስማቸው ከተሰየመው አልበማቸው መሀል “እረኛው” የተሰኘው ነጠላ ዜማ ተለቀቀ

ሙዚቃዊ በጎንደር ፋሲለደስ ባህል ቡድን ስም ከተሰየመው አልበም መሀል “እረኛዬ” የተሰኘው ነጠላ ዜማን ወደእናንተ ሲያደርስ ታላቅ ደስታ የተሰማው ሲሆን በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ይፋ ሆኗል። በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ዘርፍ ውስጥ እንደ ይርጋ ዱባለ፣ እንዬ ታከለ፣ አበበ ብርሃኔ እንዲሁም አሰፉ ደባልቄ ያሉ ዝነኞችን ያፈራው የጎንደር ፋሲለደስ ቡድን በስማቸው …

ጎንደር ፋሲለደስ የባህል ቡድን በስማቸው ከተሰየመው አልበማቸው መሀል “እረኛው” የተሰኘው ነጠላ ዜማ ተለቀቀ Read More »

የስንታየሁ በላይና የባልከው ዓለሙ ‘ይገርማል’ የተሰኘ ሁለተኛ የቅብብሎሽ ዜማ ተለቀቀ

የስንታየሁ በላይና የባልከው ዓለሙ ‘ይገርማል’ የተሰኘ ሁለተኛ የቅብብሎሽ ዜማ በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም በዲጂታል መተግበሪያዎች ተለቀቀ፡፡ በዚህ ነጠላ ዜማ ዘመናዊና ባህላዊ የኢትዮጵያ ጃዝ ይዘቶች በጋራ ሆነው ተመልካቾችን ይስባሉ የሙዚቃ መልክዓ ምድሩ ላይም ጉልህ አሻራን ያሳርፋሉ፡፡  ስንታየሁና ባልከው በቅርቡ ከሃሳቤ የተሰኘ የጋራ ዜማ/የቅብብሎሽ ዜማ ማውጣታቸው ይታወሳል፡፡ ይገርማል ቅንብሩ በእውቁ ሙዚቀኛ ግሩም መዝሙር የተሰራ ሲሆን የተለያዩ የሙዚቃ …

የስንታየሁ በላይና የባልከው ዓለሙ ‘ይገርማል’ የተሰኘ ሁለተኛ የቅብብሎሽ ዜማ ተለቀቀ Read More »

የጆርጋ መስፍን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ አልበም ሸክላን ቀድመው ይዘዙ

ሙዚቃዊ ታዋቂውን ሙዚቀኛ ፣ አሬንጀር እንዲሁም ፕሮዲውሰር የሆነውን ጆርጋ መስፍንን ሲያቀርብላችሁ ኩራት ይሰማዋል፡፡ በሙዚቃ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ መፍጠር የቻለው ጆርጋ መስፍን አሁን ደግሞ ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ በተሰኘ አዲስ አልበም ወደ እናንተ መጥቷል፡፡ ‘ ከሁሉ የላቀው ደግ’ በተለይም የኢትዮጵያ ጃዝ ሙዚቃ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ይዘቶች ጋር መንፈሳዊነትን በማዋሃድ ኢትዮ ጃዝን የሚያስቃኝ አልበም ነው፡፡  በሙዚቃዊ አማካኝነት …

የጆርጋ መስፍን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ አልበም ሸክላን ቀድመው ይዘዙ Read More »