የጆርጋ መስፍን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ ኢትዮ ጃዝ አልበም ተለቀቀ
ጆርጋ መስፍን በኢትዮ ጃዝ ዓለም እውቅ ሙዚቀኛ ሲሆን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ የተሰኘውን አልበሙን ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም በዲጂታል መተግበሪያዎች ለአድናቂዎቹ አድርሷል፡፡ ዶ/ር ሙላቱ አስታጥቄ በሞያ ኮትኩቶ ያሳደገው የጆርጋ መስፍን አልበም በተለይም የኢትዮጵያ ጃዝ ሙዚቃ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ይዘቶች ጋር መንፈሳዊነትን በማዋሃድ ኢትዮ ጃዝን የሚያስቃኝ አልበም ነው፡፡ ጆርጋ የሙዚቃ ጉዞውን …


