News Amharic

Samuel Mulugeta COO of Muzikawi signed New record deal with Balkew Alemu

​​ከአስደናቂው አርቲስታችን ባልከው አለሙ ጋር የአሳታሚነት ውል በመፈራረማችን ታላቅ ደስታ

ተሰምቶናል፡፡ ባልከው በዚህ አመት ስራዎቻቸውን ከምንለቃቸው አስራ ስድስት አርቲስቶች መሀከል አንዱ ነው፡፡ባልከው አለሙ በመጪዎቹ ጊዜያት ከታዋቂዎቹ የሙዚቃ ባለሞያዎች አንዱ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ድንቅ ባለተሰጥዖ ሙዚቀኛ ነው። ባልከው ከሙዚቃው ጎን ለጎንም የቅርብ ጓደኞቹ እንደሚመስክሩለት ጎበዝ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ነው።

The Muzikawi team at the Muzikawi Studios headquarters in Ethiopia Addis Abbaba

ጋዜጣዊ ጥቆማ: የሙዚቃዊ መክፈቻ

የኢትዮጵያን ሙዚቃ ኢንደስትሪ ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚሰራ ድርጅት ተቋቋመ
የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢንደስትሪ ወደ አለም አቀፍ ደረጃ የማሸጋገር ዓላማ ይዞ የተቋቋመው አዲሱን ድርጅታችንን “ሙዚቃዊ”ን እናስተዋውቅዎ፡፡
ድርጅታችን የተቋቋመው በሙዚቃ ኢንዱስትሪው በኢትዮጵያ ካካበተው የ17 አመታት የስራ ልምድና የ25 ዓመታት የዓለምአቀፍ ተሞክሮ መሰረት ሲሆን እ.ኤ.አ በ2022 አስራ ስድሰት ሙዚቀኞችን እና ከመቶ በላይ የሙዚቃ ስራዎች በመላው አለም ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡

Muzikawi Music Studio in Ethiopia Addis Ababa

ለአዲሱ የዲጂታል መድረክ፤ “ላይቭና ክሎዝ አፕ” በዝግጅት ላይ

ላይቭና ክሎዝ አፕ በተሰኘው አዲሱ የዲጂታል መድረካችን ተከታታይ ኮንሰርት ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ነን። በእውቁ አርቲስት ጆርጋ መስፍን ፕሮዲውስ የተደረገውና ለረጅም ጊዜ ስናዘጋጅ በከረምነው ሶስተኛው ዙር የላይቭና ክሎዝ አፕ መድረክ የሰባት አርቲስቶችን ሙሉ ስራዎች የምናቀርብ ሲሆን የመጀመሪያ ስራችንን መልቀቅ የምንጀምረው በታዋቂው አርቲስት እሱባለው ይታየው ነው፡፡