News Amharic

The legendary Artist Dawit Yifru awarded an honorary diploma!

አንጋፋው አርቲስት ዳዊት ይፍሩ የህይወት ዘመን አገልግሎት የክብር ዲፕሎማ ተበረከተላቸው!

አንጋፋው አርቲስት ዳዊት ይፍሩ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ከአምስት አስርት አመታት በላይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ፣በአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ፣ የህይወት ዘመን አግልግሎት የክብር ዲፕሎማ ተበረከተላቸው! ትላንትና በፍሬንድ ሺፕ ኢንተርናሽናል ሆቴል ከቀኑ 9፡30 እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት በዘለቀው የሽልማት ሰነ-ስርዓት ስለአንጋፋው አርቲስት በሰላም ኢትዮጵያ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም የቀረበ ሲሆን ያንን አስከትሎም የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ …

አንጋፋው አርቲስት ዳዊት ይፍሩ የህይወት ዘመን አገልግሎት የክብር ዲፕሎማ ተበረከተላቸው! Read More »

Samuel Mulugeta COO of Muzikawi signed New record deal with Anis Gabi

የአሳታሚነት ውል ከአኒስ ገቢ ጋር

በዚህ አመት አስደናቂ የኦሮምኛ ሙዚቃዎች ይደርስዎታል ከድንቁና ባለችሎታው ሙዚቀኛ አኒስ ገቢ ጋር የአሳታሚነት ውል በመፈራረማችን ደስ ብሎናል፡፡ አኒስ አስደናቂ ችሎታ ያለው ወጣት ድምፃዊ ሲሆን በዚህ አመት ስራቸውን ከምንለቃቸው አርቲስቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ የአኒስ ገቢ አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ በቅርቡ ይለቀቃል፡፡

Samuel Mulugeta COO of Muzikawi signed New record deal with Jorga Mesfin

የሙዚቃ አሳታሚነት ውል ከሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን ጋር 

ከኢትዮጵያዊው ሳክስፎኒስት እና የውዳሴ ኢትዮ ጃዝ ቡድን መስራች ጆርጋ መስፍን ጋር የአርቲስትና ፐብሊሺንግ ውል ስምምነት በመፈራረማችን ደስ ብሎናል።  ጆርጋ በኢትዮጵያና አለም አቀፍ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ላለፉት አመታት አሻራን ያስቀመጠ ሙዚቀኛ ነው። በቀጣይ ግሩም ስራዎችን ይዘን እንቀርባለን። ጠብቁን!

Samuel Mulugeta COO of Muzikawi signed New record deal with Sintayehu Belay

የአሳታሚነት ውል ከስንታየሁ በላይ  ጋር

  ደምፀ መረዋዋ የሙዚቃዊ የመጀመሪያ ሴት አርቲስት ማክሰኞ ግንቦት 17 ቀን 2022 ዓ.ም.  ከአስደናቂዋ  ድምፃዊት ስንታየሁ በላይ ጋር አዲስ የሪከርድ ስምምነት መፈራረማችንን ስናበስር በደስታ ነው። በኢንዱስትሪው ውስጥ ማራኪ ድምጽ ካላቸው ሴት ድምፃውያን መካከል አንዷ ትሆናለች ተብሎ ይጠበቃል። የመጀመሪያው ገሚስ አልበሟ በቅርብ ቀን ይለቀቃል!

«የኔ ዓለም» ገሚስ አልበም (EP) ተለቀቀ!

በ «ፈልጌ» የሙዚቃ ቪዲዮ የተዋወቃችሁት ባልከው አለሙ «የኔ ዓለም» በተሰኘ ገሚስ አልበም (EP) በድጋሜ ይዘንላችሁ በመምጣታችን ደስታ ተሰምቶናል፡፡ በዚህ ገሚስ አልበም (EP) ዘውዲቱ፣ ለፍቅር ብለን እንዲሁም የትዝታ ፈረስ የተሰኙ ወደር የለሽ ሙዚቃዎች የተካተቱ ሲሆን ግሩም መዝሙር አቀናብሯቸዋል፣ ብዙ እውቅ ሙዚቀኞችም ተሳትፈውባቸዋል፡፡ Youtube Playlist ገሚስ አልበሙን በመረጧቸው የሙዚቃ መተግበሪያዎች ያድምጡ

Samuel Mulugeta COO of Muzikawi signed New record deal with Balkew Alemu

​​ከአስደናቂው አርቲስታችን ባልከው አለሙ ጋር የአሳታሚነት ውል በመፈራረማችን ታላቅ ደስታ

ተሰምቶናል፡፡ ባልከው በዚህ አመት ስራዎቻቸውን ከምንለቃቸው አስራ ስድስት አርቲስቶች መሀከል አንዱ ነው፡፡ባልከው አለሙ በመጪዎቹ ጊዜያት ከታዋቂዎቹ የሙዚቃ ባለሞያዎች አንዱ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ድንቅ ባለተሰጥዖ ሙዚቀኛ ነው። ባልከው ከሙዚቃው ጎን ለጎንም የቅርብ ጓደኞቹ እንደሚመስክሩለት ጎበዝ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ነው።

The Muzikawi team at the Muzikawi Studios headquarters in Ethiopia Addis Abbaba

ጋዜጣዊ ጥቆማ: የሙዚቃዊ መክፈቻ

የኢትዮጵያን ሙዚቃ ኢንደስትሪ ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚሰራ ድርጅት ተቋቋመ
የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢንደስትሪ ወደ አለም አቀፍ ደረጃ የማሸጋገር ዓላማ ይዞ የተቋቋመው አዲሱን ድርጅታችንን “ሙዚቃዊ”ን እናስተዋውቅዎ፡፡
ድርጅታችን የተቋቋመው በሙዚቃ ኢንዱስትሪው በኢትዮጵያ ካካበተው የ17 አመታት የስራ ልምድና የ25 ዓመታት የዓለምአቀፍ ተሞክሮ መሰረት ሲሆን እ.ኤ.አ በ2022 አስራ ስድሰት ሙዚቀኞችን እና ከመቶ በላይ የሙዚቃ ስራዎች በመላው አለም ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡

Muzikawi Music Studio in Ethiopia Addis Ababa

ለአዲሱ የዲጂታል መድረክ፤ “ላይቭና ክሎዝ አፕ” በዝግጅት ላይ

ላይቭና ክሎዝ አፕ በተሰኘው አዲሱ የዲጂታል መድረካችን ተከታታይ ኮንሰርት ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ነን። በእውቁ አርቲስት ጆርጋ መስፍን ፕሮዲውስ የተደረገውና ለረጅም ጊዜ ስናዘጋጅ በከረምነው ሶስተኛው ዙር የላይቭና ክሎዝ አፕ መድረክ የሰባት አርቲስቶችን ሙሉ ስራዎች የምናቀርብ ሲሆን የመጀመሪያ ስራችንን መልቀቅ የምንጀምረው በታዋቂው አርቲስት እሱባለው ይታየው ነው፡፡