ብርትኳን መብራህቱ

በመቋለ ከተማ ተወልዳ ያደገችው ብርትኳን መብራህቱ ወይም ገሬዋኒ ሙዚቃን በመስማት የሙዚቃ ፍቅር ያደረባት ሲሆን ከቀን ወደ ቀን ሙዚቃን በመስማትና በማቀንቀን ራሷን ማብቃት ጀመረች፡፡ በዚህም ሰርከስ ትግራይን በመቀላቀል የተጀመረው አንድ እርምጃ የሙዚቃ ጉዞ በኦሳ ትግራይ ምግባረ ሰናይ ድርጅትን በመቀላቀል የተለያዩ ስልጠናዎችን በመውሰድና በመድረክ ላይ በመጫወት የሙዚቃን አለም በሰፊው ተቀላቅላለች፡፡

“በገሬ ቁጥር 1 እና 2” እንዲሁም “ፋዱማ” ተወዳጅነትን ያተረፈችው የመቀሌዋ ፈርጥ ብርትኳን በሙዚቃ ጉዞዋ ላይ አስር ሙዚቃዎችን ያደረሰች ሲሆን ስራዎቿ በሙዚቃ ወዳጆች ዘንድ አድናቆትን አትርፈዋል፡፡
ላለፉት አመታት በትግራይ ክልል በነበረው ችግር ምክንያት ከምትወደው ሙዚቃ ጋር ተራርቃ የቆየችው ብርቱካን በአሁን ሰዓት በአዲስ ስራ መጥታለች፡፡ ስለምትወደው ሙዚቃም እንዲህ ብላ ትናገራለች።

ሙዚቃ መግባቢያ ቋንቋ ነው ስሜቴንም የምገልጽበት ነው

ብርትኳን መብራህቱ

ስለ አዲሱ “ሽሕ ምውላድ” ስለተሰኘው ነጠላ ዜማዋ ስትናገር “በአማርኛ ውለድልኝ የሚል ስያሜ ያለውና ስለ አንድ ጀግና ወንድ የሚናገር ሙዚቃ ሲሆን ልክ እንደ ራስህ ጀግና ልጅ ውለድልኝ የሚል አንድምታ አለው” ትላለች።

ጉዋይላ የተሰኘውን የትግራይ ባህላዊ የሙዚቃ ምትን ልዩ ከሆነው ባቲ ጋር ያዋሀደው ይህ ስራ ባህላዊውን ሙዚቃ ከዘመናዊው ጋር ባማረ መልኩ አጣጥሞታል፤ ባህላዊውን ከበሮ ከዘመናዊው ጋርም አጣምሯል። ይህም ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ ለአለም አቀፍ የሙዚቃ ወዳጆች ተደራሽ እንዲሆን ያደርገዋል።

ይህ ነጠላ ዜማ በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም አለም አቀፍ መተግበሪያዎች ይገኛል።

‘’ሽሕ ምውላድ’’ የሙዚቃ ቪዲዮ

የሚመርጡትን የሙዚቃ አገልግሎት ይምረጡ

Social media links