ባልከው አለሙ
ባልከው አለሙ በመጪዎቹ ጊዜያት ከታዋቂዎቹ የሙዚቃ ባለሞያዎች አንዱ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ድንቅ ባለተሰጥዖ ሙዚቀኛ ነው። ባልከው ከሙዚቃው ጎን ለጎንም የቅርብ ጓደኞቹ እንደሚመስክሩለት ጎበዝ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ነው።
የአይን ብርሀኑን በልጅነቱ ያጣው ባልከው ብርሀኑን ማጣቱ ድንቅ ስራን ከመስራትና የሚወደውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አልጎተተውም፡፡ባልከው ለሙዚቃ ኢንዱስትሪው አዲስ አይደለም ከዚህ በፊት ‹‹በኢትዮጵያ አይደል›› ውድድር ግዜ በአስገራሚ ድምጹ አሁን በጉጉት ከሚጠብቁት አድናቂዎቹ ጋር ተዋውቋል፡፡
በሙዚቃ ውስጥ ስሜቴን በነጻነት የማካፍለው ጓደኛዬን አግኝቻለሁ"
አሁን የሚለቀቀውን ነጠላ ዜማ እንዲሁም ቀጣይ የሚለቀቀው ግማሽ አልበም (EP) ላይ ግሩም መዝሙር፣ ዳዊት ነጋና አለማየሁ ደመቀን ጨምሮ ድንቅ አርቲስቶች የተሳተፉበት ሲሆን በአብዛኛው ሙዚቃዎቹ የ60ና 70ዎቹ ስሜት ውስጥ የሚነሳ እና የኢትዮ ጃዝና የምእራብ አፍሪካ ሪትም ፅንሰ-ሀሳብ ከዘመናዊው ሙዚቃ ጋር ውህደት የፈጠሩበት ድንቅ ስራ ነው፡፡
ግሩም ሆኖ የተጻፈው ግጥም, ከውብ ዜማ ጋር እንዲሁም ካማረ ቅላጼ ጋር ታሽቶ የዘመናችንን የሙዚቃ ደረጃ ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ደርገዋል፡፡