ሀብታሙ ተድላ

ሀብታሙ ተድላ የሙዚቃ ጉዞውን የጀመረው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን ካጠናቀቀ በኋላ በፍካት ትያትርና የሙዚቃ ቡድን እንዲሁም ሰርከስ ጎንደር ሲሆን ዘግየት ብሎ ግን የመከላከያ ኦርኬስትራን በመቀላቀል፤ ፕሮፌሽናል ክህሎትን አዳብሯል::

ሀብታሙ በሙዚቃ ጉዞ ውስጥ ጉልህ ስኬቶችን ያገኘ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ችሎታውን ያስመሰከረባቸው ኢትዮጵያን አይድልና ፋና ላምሮት ይጠቀሳሉ፡፡ አሁን ከኢትዮ ከለር ጋር በመሆን በፈንድቃ በድምፃዊነት ፣በፌዴራል ፖሊስ ኦርኬስትራ እንዲሁም ሆሚ፣ትሪፕል ሆቴልና ዮያ በተሰኙ የምሽት ክበቦችም በትግርኛ፣አፋን ኦሮሞ፣ኮንሶ፣ጋምቤልኛና ሱማሊኛ ቋንቋዎች የተለያዩ ሙዚቃዎችን ይጫወታል፡፡

ጎንደር’ ፣ ‘አልናገር’ እና ‘የወሎ ልጅ’ በሚባሉት ነጠላ ዜማዎቹ የሚታወቀው የሀብታሙ ‘አወይ የኛ ነገር’ የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዜማውን በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ፍቅር ለምን ይቀዘቅዛል የሚል ኃሳብ በማንሳት ‘አንድ ላይ እየኖርን ለምን ፍቅራችን ቀነሰ?’ የሚል ጥያቄ ይጠይቃል::

በሳክስፎኒስቱና አቀናባሪው ጆርጋ መስፍን የተቀናበረው የሀብታሙ ‘አወይ የኛ ነገር’ የተሰኘው አዲሱ ነጠላ ዜማ ባህላዊ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ምቶች ከዘመናዊ ጃዝ ይዘቶች ጋር በግሩም ሁኔታ ያዋህዳል፡፡ ሙዚቃው ‘ችክችካ’ በተሰኘው ዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ አማካኝነት የተመሰረተ ሲሆን ይህም የሙዚቃ ምት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ወሳኝ የሚባል ነው፡፡

አርቲስት ሀብታሙ የሙዚቃውን ግጥም ያዘጋጀው ሲሆን ሌሎች እውቅ ሙዚቀኞች በስራው ላይ ተሳትፈዋል።

‘’አወይ የኛ ነገር’’ የሙዚቃ ቪዲዮ

የሚመርጡትን የሙዚቃ አገልግሎት ይምረጡ

Social media links