ጎንደር ፋሲለደስ የባህል ቡድን በስማቸው ከተሰየመው አልበማቸው መሀል “እረኛው” የተሰኘው ነጠላ ዜማ ተለቀቀ

ሙዚቃዊ በጎንደር ፋሲለደስ ባህል ቡድን ስም ከተሰየመው አልበም መሀል “እረኛዬ” የተሰኘው ነጠላ ዜማን ወደእናንተ ሲያደርስ ታላቅ ደስታ የተሰማው ሲሆን በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ይፋ ሆኗል።

በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ዘርፍ ውስጥ እንደ ይርጋ ዱባለ፣ እንዬ ታከለ፣ አበበ ብርሃኔ እንዲሁም አሰፉ ደባልቄ ያሉ ዝነኞችን ያፈራው የጎንደር ፋሲለደስ ቡድን በስማቸው ከተሰየመው አልበም ላይ እረኛው የተሰኘውን ነጠላ ዜማቸውን አውጥተዋል፡፡ በአስፋው መለሰ ግጥምና ዜማው የተደረሰው እንዲሁም በዳንኤል ለይኩን ቅንብሩ የተሰራው ‘’እረኛው’’ የእረኛንና የአንዲት ሴትን ፍቅር የሚገልፅ ነው።

የጎንደር ፋሲለደስ የባህል ቡድን በጽናት፣ፈጠራ እንዲሁም ኪነ ጥበባዊ ልህቀት የታጀቡ የሚያስደቁ ጊዜያትን ሲያሳልፍ በ1977 ዓ.ም ታግሎ አታጋይ ተብሎ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ቡድኑ በኢትዮጵያ ባህል ውስጥ እራሱን ዝነኛ ዘላቂነት ያለው የባህል ቡድን አድርጎ ለማቆየት በርካታ ተግዳሮቶችን አልፏል፡፡ 

የጎንደር ፋሲለደስ የባህል ቡድን ‘ጎንደር ፋሲለደስ’ ከተሰኘው አልበማቸው ላይ እረኛው የተሰኘው ነጠላ ዜማቸው በተለቀቀበት በዚህ ወቅት የቀደምት የስራ ባልደረቦቻቸውን ዝና አጉልተው ከማሳየት በተጨማሪም ወደ ፊት የሚጓዙበትን ልዩ መንገድ የሚቀርፁ ይሆናል፡፡