የአኒስ ገቢ የ2015ቱ አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል ሙሉ የመድረክ ላይ ስራ ተለቀቀ!

የአኒስ ገቢ የ2015ቱ አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል ሙሉ የመድረክ ላይ ስራ በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል ላይ ይገኛል! በስዊድን ኤምባሲ የተካሄደው ይህ ፌስቲቫል የአኒስ ልዩ ችሎታ የታየበት ሲሆን አኒስ ነጠላ ዜማው የሆነውን ‘’ሀደ ሚልኪ’’ ን፣የአባቱ ገቢ ኤደኦ ተወዳጅ የሆነውን ‘’ወል መሌ ማል ቀብና’’  እንዲሁም ጊዜ የማይሽረው የዶ/ር አሊ ቢራ ‘’ገመቹ’’ የተሰኙትን ዜማዎች ለህዝብ አቅርቧል፡፡

ታዳሚዎች በአኒስ ቀልብን በሚገዛ የመድረክ ላይ አቀራረብ ተማርከው አብረው ሲያዜሙ እንዲሁም ሲወዛወዙ የተስተዋሉ ሲሆን የጃዝ ስሜት ያለው የአኒስ ‘’ሀደ ሚልኪ’’ የተሰኘ ዜማ ከፌስቲቫሉ ጭብጥ ጋር አብሮ የሚሄድ የነበረና ለዝግጅቱ ጣዕም የሰጠ ነበር፡፡

አኒስ በ2014 ዓ.ም ከሙዚቃዊ ጋር  ባወጣው ‘’ሀደ ሚልኪ’’ የተሰኘ ነጠላ ዜማ የብዙዎችን ቀልብ መማረኩ አይዘነጋም፡፡ ይህ እራሱ አኒስ ያቀናበረውና ጆርጋ መስፍን ሪ-አሬንጅ ያደረገው ዜማ አኒስን በሃጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ላይ ምርጥ አቀናባሪ በሚል ዘርፍ እንዲያሸንፍ ሲያደርገው ምርጥ ዘመናዊ ዜማ እንዲሁም ምርጥ ወንድ አርቲስት በሚለው ዘርፍ ደግሞ እንዲታጭ አድርጎታል፡፡

በሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም አኒስ ሁለተኛ ነጠላ ዜማው የሆነውን ‘’ኮቱሜ’’ ከሙዚቃዊ ጋር በመሆን ለህዝብ አድርሷል::

ወደ ሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል በማምራት የአኒስን የ2015ት ሙሉ የአዲስ ጃዝ ፌስቲቫል የመድረክ ላይ ስራ እንድትመለከቱ እንዲሁም በቅርብ ጊዜ ለአድማጮች ያደረሰውን ‘’ኮቱሜ’’ የተሰኘ ነጠላ ዜማውን በተጨማሪም ‘’ሀደ ሚልኪ’’ ን እንድታደምጡ ጋበዝን፡፡