የሬከርድና የፐብሊሺንግ ውል ከአዝማች የሂፕ ሆፕ ቡድን ጋር

ከአዝማች የሂፕ ሆፕ ቡድን ጋር አዲስ የሬከርድና የፐብሊሺንግ ውል

“አዝማች” የሂፕ ሆፕ ቡድን የሬከርዲንግና የፐብሊሺንግ ውል ከሙዚቃዊ ጋር ተፈራረመ።

ሶስት ሙዚቀኞችን ፣ ሰናይ መኮንን፣ ቤርሳቤህ አማረ (ናኒ) እንዲሁም ቴዎድሮስ ምናሉ (ልጅ ቴዲ)ን በውስጡ የያዘው ቡድኑ ከሙዚቃዊ ጋር በጋራ በመሆን በይዘትም በአቀራረብም ቆንጆ ስራዎችን ያዘጋጀ ሲሆን ወደ ህዝብ ጆሮ ለማድረስ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ቡድኑ የቀደምት ሂፕ ሆፕ እንዲሁም የኢትዮጵያ የሙዚቃ ምቶችና ዜማዎች ተጽእኖ በከፍተኛ ሁኔታ ያረፈበት መሆኑ ከሌሎች የሂፕ ሆፕ ቡድኖች የተለየ ያደርገዋል፡፡ የቡድኑ የዘፈን ግጥም ወጣቶችን ለማረበታታት አገር በቀል ታሪኮችን የሚናገሩ ናቸው፡፡ ቡድኑ በ2008 ዓ.ም ከተቋቋመ ጀምሮ እንደ ፕሮቶጄ (JAM) ማይክ ኤሊሰን (USA) ኤደን ደርሶ (ISR) ዳንኤል ለማ (SWE) እና AKALA (UK) ከተሰኙ ዓለም አቀፍ አርቲስቶች ጋር መድረክ ተጋርቷል፡፡