እውቁ ሙዚቀኛ ኪሮስ ግርማይ ‘ናፍቆት’ የተሰኘው ነጠላ ዜማውን ለአድማጮች አደረሰ

በውቅሮ ትግራይ የተወለደው ኪሮስ ግርማይ ‘ናፍቆት’ የተሰኘው አዲሱ ነጠላ ዜማውን ለአድማጮች አድርሷል፡፡ ልጅ
እያለ ምንም እንኳን የሙዚቃ ፍቅሩ የቤተሰብ ድጋፍ ባያገኝም በልጅነቱ ለውዝዋዜ የነበረው ፍቅር ወደ ጥልቅ የሙዚቃ ፍቅርና
ሞያ ሊያድግ ችሏል፡፡ ኪሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ውቅሮ በሚገኘው በከነማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በአጋዚ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የተከታተለ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለ ከቅድስተ ማርያም ኮሌጅ የኪይ ቦርድና
የድምጽ ስልጠና በመውሰድ የሙዚቃ ክህሎቱን አዳብሯል፡፡ ከዛም በኋላ ከድምጽ እስከ ሳውንድ ኢንጅነሪንግ ያሉ ስልጠናዎችን
ከትግራይ ቱሪዝም ቢሮ፣ ከብሔራዊ ትያትር እንዲሁም ከሰላም ኢትዮጵያ ወስዷል፡፡


የኪሮስ ተሰጥኦ በ2004 ዓ.ም በ104.4 ኤፍ ኤም የሬዲዮ ጣቢያ ላይ በተካሄደ የድምጻውያን ውድድር ላይ ተሳትፊ ምርጥ አስር
ውስጥ በገባ ጊዜ ጎልቶ ሊታይ ችሏል፡፡ የሙሉ ጊዜ ሙዚቀኛ የሆነውና በአማርኛ፣ ሱማሊኛ፣ ኮንሶ፣ አፋርኛና አፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎችን የሚጫወተው ኪሮስ  በኢትዮጵያ የተለያዩ መድረኮች ላይ ተጫውቷል፡፡

‘ናፍቆት‘  የተሰኘው ነጠላ ዜማ ጉዋይላ በተሰኘ በትግራይ ባህላዊ የሙዚቃ ምት ላይ የተመረኮዘ ሲሆን ይህም የሙዚቃ  ምት ለየት
ያለ በመሆኑ ይታወቃል፡፡ የሙዚቃው ፕሮዳክሽን የቀጥታ ቀረጻን፣ ዘመናዊውን እንዲሁም በእጅ የሚመታውን ከበሮ
በጋራ ያዋሃደ ሲሆን ይህም አካሄድ ፕሮዲውሰሮች በተለምዶ የኤሌክትሮኒክስ ከበሮ ምት ከሚጠቀሙበት አካሄድ የተለየ ነው፡፡
የተፈሪ አሰፋ ከበሮ አጨዋወት ከባህላዊ ከበሮና ክራር ድምጾች ጋር ተቀላቅለው ልዩ ድምጸት ይፈጥራሉ፡፡ ኪሮስም በዚህ ነጠላ
ዜማው ጥልቅ ተሰጥኦውን ግሩም በሆነውና ቅላፄያዊ ጥልቀት ባለው ድምጹ አሳይቷል፡፡