በሙዚቃዊ ፕሮዲውስ የተደረገው ‘’አዲስ ቀን’’ የሙዚቃ ቪዲዮ ተለቀቀ

‘’አዲስ ቀን’’ ነጠላ ሙዚቃ  በሲሳይ ጌታሁንና በርካታ አባላቶቹ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት እንዲሁም መካነየሱስ የጃዝ ትምህርት ቤት (ሴሚናሪ) ሙዚቃን በተማሩት ዙምባራ የተሰኘው ባንድ አባላት የተሰራ ነው፡፡ 

የባንዱ አባላት አሁን እንደ ቡድን በጋራ ባይሰሩም በርካቶቹ በእውቅ ባንዶች፣ የሀይማኖት ቦታዎች እንዲሁም ሌሎች የሙዚቃ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚሰሩ የሙሉ ጊዜ ሙዚቀኞች ናቸው፡፡ ‘’አዲስ ቀን‘’ ሙዚቃ የዙምባራ ባንድ አባላት በቡድን የሰሩት የመጀመሪያ ስራቸው ነው፡፡ የ ‘’አዲስ ቀን’’ መልዕክት ተስፋ እንዲሁም አዲስ ቀን ሲሆን የተለያዩ የሙዚቃ ብቃቷን ያሳየችበት ነው፡፡ ሄኖክ መሀሪ በሙዚቃው ላይ በዳይሬክተርነት፣ ኪሩቤል ተስፋዬ በሚክሲንግና ማስተሪንግ፣ ሙዚቃውን በማቀናበር ደግሞ የባንዱ አባላት በጋራ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡ የሙዚቃ ቪዲዮው በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም በሁሉም የሙዚቃ መተግበሪያዎች ተለቋል፡፡