Ibex Band

የሚመርጡትን የሙዚቃ አገልግሎት ይምረጡ​

አይቤክስ ባንድ በጆቫኒ ሪኮ እና ሰላም ወልደማርያም መሪነት እንደ አስቴር አወቀ፣ግርማ በየነ፣ጥላሁን ገሰሰ፣ሙላቱ አስታጥቄ እና መሃሙድ አህመድ ያሉ አንጋፋ አርቲስቶችን ጨምሮ ኧረ መላ መላ ለተሰኘው ዝነኛ አልበም የጀርባ አጥንት በመሆን ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ብለን የምንጠራውን ሙዚቃ ቅርጽ አስይዟል፡፡ ይህ የ1968   ዓ.ም አልበም በዛ የታሪክ ትሩፋት ውስጥ ዋና ሚና የተጫወተ ሲሆን አሁን ደግሞ ታሪክን በአግባቡ ለማሳወቅ መጥቷል፡፡

ሙሉ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ያቀፈው እና የተሟላ ባንድ የሆነው፤ ዘግይቶ ሮሃ ባንድ ወደ መሆን የተሸጋገረው አንጋፋው የአይቤክስ ባንድ በኢትዮጵያ የሙዚቃ መልክዓ ምድር ከሰባዎቹ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የሚገኙ ታላላቅ ኮከቦች ሙዚቃዎችን በመቅረጽ ዋና ሚና የተጫወተ ሲሆን ወርቃማ ስራቸውም በእውነቱ አልጠፋም/አልተዳከመም፡፡ እንደ አስቴር አወቀ፣ግርማ በየነ፣ጥላሁን ገሰሰ እንዲሁም ሌሎች ታላላቅ ድምጻውያን የጀርባ አጥንት በመሆን ያገለገለው እና መሃሙድ አህመድ እና ሙላቱ አስታጥቄ በየግላቸው የሰሩትን የሙዚቃ ስራዎች ያጀበው የአይቤክስ ባንድ አመጣጥ/ስረ መሰረት ገና በሚገባ አልተነገረም፡፡

ጆቫኒ ሪኮ እና ሰላም ወልደማርያም በ1970 ዓ.ም በድሬዳዋ፣ኢትዮጵያ

ፎቶ ከሰላም ወልደማርያም

የኢትዮጵያን ሙዚቃ ገጽታ ሁለት የተሳሳቱ አረዳዶች ሰቅዘው ይዘውታል፤ አንደኛው አረዳድ የኢትዮጵያ ሙዚቃ በተወሰነ መልኩ ስላልተበዘበዘ ንጹህ ነው የሚል ሲሆን ሌላው ደግሞ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ባህላዊ ነው የሚል ነው፡፡ ከጅማሬው/ሲጀመር በ60ዎቹ መጀመሪያና 80ዎቹ አጋማሽ የነበሩ የፖለቲካ ለውጦች ከተጋረጠባቸው እጅግ ከፍተኛ ችግር የተነሳ እጅግ ቁርጠኛ የሆኑና የተካኑ ሙዚቀኞ ብቻ ታግለው የሚቀጥሉበትና የሚሰማሩበት የሙዚቃ ሞያ እንዲፈጠር ምክንያት ሆነ፡፡ ሙሉ የአይቤክ ባንድ በጆቫኒ ሪኮ እና በሰላም ‘’ሰላሚኖ’’ ስዩም ወልደማርያም መሪነት በ70ዎቹ አጋማሽ የነበረው ደማቅ የሙዚቃ ትዕይንት መነሻዎች እንደሆኑ ይነገራል ሁለቱ ሙዚቀኞች ባንዱን በከባድ ጊዜያት ወቅት በቀዳሚነት የመሩ ብቻ ሳይሆን የ 6/8 የችክችካ ምትን ያዘመኑ ናቸው፡፡ ጆቫኒ ጠንከር ያለ የጊታር ቤዝ ላየንን በመጠቀም የሙዚቃ ምት መሰረቱን የጣለ ነው፤ ይህም እንደ ዳንስ ሙዚቃ ያሉ ባህላዊ ዜማዎችን በድጋሚ የፈጠረ ሲሆን ከሰላሚኖ አዲስ/ልዩ የጊታር አጨዋወት ዘዴ ጋር በጋራ ከአበጋዝ ክብረወርቅ ሺኦታ እስከ ሄኖክ ተመስገን ያሉ በርካታ ሙዚቀኞች ላይ ተጽእኖ ማሳረፍ ችለዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ የጆቫኒ ፌንደር ቤዝና (በፌንደር የሙዚቃዊ መሳሪያ ኮርፖሬሽን የተመረተ ጊታር) የሰላሚኖ ጊብሰን ጊታር ወጣት ሙዚቀኞች የሚመርጡት የሙዚቃ መሳሪያ ላይ ሳይቀር ተጽእኖ ማሳረፍ የቻለ ነበር፡፡ ጆቫኒና ሰላሚኖ ከሙዚቃ መሳሪያ ምርጫ ባለፈ በሙዚቃ ድምጽም ጭምር ወጣት ሙዚቀኞች ላይ ተጽእኖ አሳርፈው ነበር፤ የዲጂታል አብዮት የኢትዮጵያን ሙዚቃ ሲቀላቀል  በርካታ ተወዳጅ ሙዚቃዎች ዋና ቅላጼያቸውን የወሰዱት በአይቤክስና ሮሃ ከተሰሩ ሙዚቃዎች ነበር፡፡

 

አይቤክስ ባንድ ሶውል ኤኮስ ባንድ የሚባለው በሃምሳዎቹ የነበረው ባንድ ሲፈርስ የተቋቋመ ሲሆን  ጆቫኒና ሰላሚኖን ወደ ባንዱ በማካተት ለጥቆም የሙዚቃ ቅላጼውን ከተለያዩ እንደ ሞታውንና ዘ ቢትልስ ካሉ ተጽእኖ አሳራፊዎች በመውሰድ ከባህላዊ አማርኛ ሙዚቃ ጋር በመቀላቀል ስራውን የጀመረ ባንድ ነው፡፡ በጊዜው ከነበሩ በርካታ ባንዶች በተለየ መልኩ እርስ በእርስ ጥብቅ ወዳጅነትን የመሰረቱ ሙዚቀኞችን የያዘው አይቤክስ አስራ አምስት ወይም አስራ ስድስት አባላቶች ካሏቸው ባንዶች ጋር ሲነጻጸር በሙዚቃ ጉዞው በሙሉ ከስድስት እስከ ሰባት አባላትን ብቻ አቅፎ ዘልቋል፡፡ የአጨዋወት ስልታቸው አንድ ነገር ላይ በእጅጉ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነገር ግን በኢኮኖሚ ረገድ ወጪ የሚያስወጣ ነበር፡፡ በእጃችሁ የሚገኘውን አልበም ከመቅረጻቸው አንድ አመት ቀደም ብሎ ጆቫኒና ሰላሚኖ ለተወዳጅ የኢትዮጵያ ሙዚቃዊ መዝገብ  ቃላት አስተዋጽኦ ያደረጉ ሲሆን ይህም ተወዳጅ የሆነውን የሙዚቃ አይነት ለይቶ ያሳየ ነበር ከነዚህም ውስጥ የባንዱ አባል የሆነው መሀሙድ አህመድ  ለብቻው የሰራቸው የሙዚቃ ስራዎቹን እንዲሁም የማስታወቂያ እረፍት ድምጾችንና የ1968ቱ ኧረ መላ መላ የሚል ስያሜ ያሰጣቸውን  ኧረ መላ መላ የተሰኘውን አልበም አሬንጅ ማድረግና መቅረጽ ይጠቀሳሉ፡፡

ፎቶ ከሰላም ወልደማርያም

ሰላሚኖ  የተካነ መሪ ጊታሪስት በማድረግ ብቻ እራሱን አልገታም ፤ሁልጊዜም የታሪክ ተማሪ በመሆን ዘለቀ እንጂ፡፡ በዚህም የተነሳ በጊታር ጨዋታውና ቅንብሮቹ በርካታ የሙዚቃ ቁንጮ የሆኑ ዘመናዊ ኢትዮጵያዊ ሙዚቃዎችን ያበረከተውን ያህል በጊዜው/በዘመኑ ስለነበሩ ወይም ስለዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የጠለቀ መረዳትም እንዲኖር አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ የሰላሚኖ አስተዋጽኦ መላ ባንዱን የሚወክል ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓትም አዲስ፣ የሚያስደንስ እና ከጊዜው ጋር የሚሄድ በጆቫኒ የቤዝ ጊታር ላይ የተመሰረተ ድምጽ ፈጥሯል በዚሁ ጊዜም ሌሎች በሙዚቃው ዓለም ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በመደገፍ አጠቃላይ የሙዚቃውን ዓለም ከፍ አድርጓል ከዛ በተጨማሪም የሙዚቃ አረዳድን አሳድጓል፡፡

አይቤክስና ሮሃ ግንባርቀደም የነበሩበትን የሙዚቃ ከፍታ ጊዜያትን የተሻሉ ጊዜያት እንደነበሩ አርጎ የመውሰድ ፍላጎት አለ ይህም አሳማኝ ነው ምክንያቱም በርካቶቹ በዛን ጊዜ የነበሩ ሙዚቃዎችን አሁን ለማግኘት አስቸጋሪ ስለሆነ ነው፡፡ የአይቤክስ ፈጠራ ከበርካታ በጊዜው ከነበሩ ምዕራባውያን ባንዶች ጋር ሲነጻጸር በምንም የማይተናነስ ነበር፡፡ አይቤክስ በ60ዎቹና 70ዎቹ ከ250 አልበም ወይም 2500 ዜማዎች በላይ በመቅረጽ ለህዝብ በማድረሱ ብቻ ‘’በመዝናኛው ዘርፍ ከሁሉ የላቀ ታታሪ ሰራተኛ’’ የሚለውን ማዕረግ ከጄምስ ብራውን ሊወስድ ይችል ነበር፡፡ የተወሰኑት ሙዚቃዎች አሁን በካሴት መልክ ብቻ የሚገኙ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በጭራሽ ሙሉ አልበም ሆነው አልተለቀቁም የተወሰኑት ደግሞ አሁን ለማግኘት አዳጋች ናቸው፡፡ ከዚህ አንጻር ስንመለከተው የ 1968 ዓ.ምቱ  የኢንስትሩመንታል ሪከርዲንግ  አሁን መገኘቱ እንደ ተዓምር የሚቆጠር ነው፡፡ እጅግ በጣም በጥሩ ሁኔታ በክሮም ካሴት ላይ ይህ ሙዚቃ መገኘቱ የሙዚቃን ታሪክ ሕያው በማድረግ መጪውን ዘመን የሚያስተካክል ነው፡፡  ስቴርዮ ኢንስትሩመንታል ሙዚቃ የተቀረጸው ቮይስ ኦፍ ዘ ጎስፕል ለተሰኘው ሬዲዮ ይሰራ ከነበረው ስዊድናዊው ካርል ጉስታቭ ጋር በኅብረት ነው፡፡ የሙዚቃ ቀረጻው በአዲስ አበባ በሚገኘው ራስ ሆቴል የሙዚቃ አዳራሽ ሁለት የቅጂ ጊዜያትን ብቻ ነው የፈጀው፡፡ አይቤክስ ባንድ ባለአራት ረድፍ መቅረጫ ለመጠቀም በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባንድ ነበር መቅረጫውም የተገኘው ከካርል ጉስታቭ በተውሶ ሲሆን በአገሪቱም የመጀመሪያው ባለአራት ረድፍ መቅረጫ ነበር፡፡ በዛው ሳምንት ዘግየት ብሎ ጆቫኒና ሰላሚኖ የተቀረጸው ሙዚቃ እነሱ የፈለጉትን ያህል ብዛት እንደሌለው ተገነዘቡ ስለዚህም በአንድ ረድፍ መቅረጫ አንድ ተጨማሪ የመቅረጫ ጊዜ በመውሰድ ተጨማሪ አራት ሙዚቃዎችን ቀረጹ፡፡ አይቤክስ ባንድ በቋሚነት ስራውን የሚያቀርብበት ራስ ሆቴል እና ግዮን ሆቴል በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ በተለይም ለአዲስ አባባ  ከጥቂት አመታት በፊት ሞታውን ለአሜሪካና ለዲትሮይት የነበረውን አይነት ስፍራ ነበራቸው ማለትም ለሙዚቃ ፈጠራና ለመድረክ ስራ ዋና መናኃሪያ ነበሩ፡፡

ላለፈው ግማሽ ምዕተ አመት ስለነበረው የኢትዮጵያ ሙዚቃ እጅግ አስገራሚው ነገር ባህል እና ዘመናዊነት የተቆራኙበት/የተሳሰሩበት መንገድ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ‘’ወርቃማ ጊዜ’’ ነበር ወይስ አልነበረም ለማለት ወይም መቼ ነው ወርቃማ ጊዜ ላይ ያለነው የሚለውን ለመናገር ጥቂት አስቸጋሪ ነው፡፡ ቀደም ሲል የተሰሩ በርካታ ሙዚቃዎች በሚያሳዝን ሁኔታ ችላ ተብለዋል ነገር ግን ቀደም ሲል በነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ የበፊቱ ጊዜ ወርቃማ ጊዜ ነበር ማለት ነገሮችን እጅግ ማቃለል ይሆናል፡፡ እንዲያውም ለመጀመሪያ ጊዜ የቀድሞዎቹም የበፊቶቹም ስራዎች ተደራሽ በመሆናቸው አሁን እየደረስንበት ያለነው ዘመን ነው ወርቃማ ጊዜ ሊሆን የሚችለው፤ የከዚህ ቀደም ታላላቅ አበርክቶዎችም ዛሬ ላይ ያበበ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ እንዲኖር ጠንካራ መሰረት መጣል ይችላሉ፡፡ አይቤክስ ባንድ የቀድሞው፣ አሁን ያለው እንዲሁም የወደፊቱ ዘመን ላይ በጠንካራ ሁኔታ ቆሞ ይገኛል ወርቃማ ከተባለም መባል ያለበት ይህ ሁኔታ ነው፡፡

የስቴሪዮ ኢንስትሩመንታል ሙዚቃ ዝርዝር ታሪክ በበርካታ መልኩ ልዩ ነው፡፡ በመጀመሪያ ባለአራት ረድፍ መቅረጫዎች  ስላልነበሩ ቀደም ብሎ መቀረጽ አይችልም ነበር ዘግይቶም ቢሆን ቢያንስ ቀጥለው በመጡት ጥቂት አመታትም ሊመዘገብ አይችልም ነበር ይህም የሆነበት ምክንያት የሙዚቃው ዓለም የዛኔ ስልጣን የያዘው የደርግ መንግስት እንዲሁም ሌሎች ተቀናቃኝ ቡድኖች የበላይነታቸውን ለማረጋገጥ በሞከሩ ጊዜ በተፈጠረው ምቹ ባልነበረው የፖለቲካ ሁኔታ በደረሰበት ጉዳት እንዲሁም ከቮይስ ኦፍ ጎስፕል ሬዲዮ በውሰት የመጡት የሙዚቃ መሳሪያዎች የሬዲዮ ጣቢያው በ 1970 ዓ.ም ሲዘጋ ከኢትዮጵያ በመጥፋታቸው ነው፡፡ በቀረጻ ወቅት እገዛ ያደረገው በጊዜው ከኢትዮጵያ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን መካነ እየሱስ ጋር በጋራ ይሰራ የነበረው ስዊድናዊ ካርል ጉስታቭ ለንድግረን የራስ ሆቴል አስተዳደርም ሆነ ባለስልጣናት ሳያውቁ የድምጽ ማጉያ ለማስተካከል የነበራቸው ጊዜ አስራ አምስት ደቂቃዎች ብቻ እንደነበር በተለይም ደግሞ እኩለ ለሊት ላይ የሰዓት እላፊው ከመጀመሩ በፊት ቀረጻውን ለመጨረስ ያደርጉት የነበረውን ጥረት ያስታውሳል፡፡ ድምጻቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመቅዳት ቀደም ሲል ያልነበሩ መሳሪያዎችን የመጠቀም እድል እንዳያመልጣቸው እና የመጓጓዣ ተግዳሮቶችን በጃቸው ባሉ ነገሮች ለመፍታት በሚሞክሩ ጊዜ አይቤክስ ባንድ እንደ ባንድ ለረዥም አመታት ለመቆየት የቻሉባቸውን የፈጠራ ችሎታ/ዘመናዊነት እና ነገሮች በተለዋወጡ ቁጥር ከተለዋወጡት ነገሮች ጋር እራሳቸውን አስማምተው ለመጓዝ የመቻላቸውን ሁኔታ/ከጊዜ ጋር የመጓዝ ችሎታቸውን አሳይተዋል፡፡ የስቴሪዮ ኢንስትሩመንታል ሙዚቃ ሪከርዲንግ በሚታወቅ በአንድ ወቅት የተከናወነ ቢሆንም ከዘመናት በፊት የተካሄደ ይመስላል፡፡

ስቴሪዮ ኢንስትሩመንታል ሙዚቃ ከወጣበት ስፍራ የወጣው በርካታው ኃይል/ኢነርጂ ጠፍቷል ወይም ደግሞ ኢትዮጵያ ከ1960ዎቹ መጨረሻ አንስቶ እስከ 80ዎቹ መጀመሪያ ባሳለፈችው የማህበራዊ ለውጥ ወቅት የትኩረት አቅጣጫው ተቀይሷል፡፡ ምንም እንኳን መሪዎች አብዮታዊ መሆናቸውን ቢለፍፉም የአይቤክስ ባንድ የስራ ሥነ-ምግባር ግን እውነትም አብዮታዊ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አይቤክስ ባንድ ስራውን በፍጹም አላቋረጠም ከጊዜው ጋር መጓዝ ጀመረ እንጂ/ተጓዘ እንጂ፤ አፍሪካ፣ አውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅ በስፋት የሙዚቃ ጉዞ አድርጓል፤ በርካታ የሙዚቃ ስራዎች ላይ ገደብ ያሳረፈውን የሰዓት እላፊ በማይነካ ሁኔታም የሚሰራበትን መንገድ ፈጥሯል፡፡ ምንም እንኳን የሰዓት እላፊ ገደቡ እና እገዳዎች ቢኖሩም አይቤክስ በ1970ዎቹ እጅግ ትልልቅ መድረኮች ላይ ተጫውቷል፡፡ የባንዱ ሙሉ የታሪክ ትሩፋት በጭራሽ ተነግሮ አያውቅም ፤የሙዚቃ ስራዎቹ ግን ከቃላት በላይ ይናገራሉ ስለዚህም የአይቤክስ ባንድ ስቴሪዮ ኢንስትሩመንታል ሙዚቃን እንድታደምጡ ጋብዘናችኋል፡፡

ሙዚቀኞች፡                           መሳሪያ

ሰላም ወልደማርያም –            ሊድ ጊታር

ጆቫኒ ሪኮ –                             ባስ

ደረጄ መኮንን –                    ኪይ ቦርድስ

ተስፋዬ መኮንን –                   ድራምስ

ፍቃዱ አምደመስቀል –            ሳክሶፎን እና ፍሉ

ቴድሮስ ምትኩ –                   ሳክስፎን እና ፍሉት

ግርማ ጪብሳ –                          ኮንጋስ


ሁሉም ሙዚቃዎች በጆቫኒ ሪኮ እና ሰላም ወልደማርያም የተደራጁና የተዘጋጁ ናቸው

 

በአዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ በሐምሌ ወር 1968 ዓ.ም ተቀረጸው

የቀረጻ ኢንጅነሮች፡ ካርል ጉስታቭ ለንድግረን (ከትራክ 1-8/ከ 1-8 ያሉትን ሙዚቃዎች)፣ አይቤክስ ባንድ (ትራክ 9-12/ከ9-12 ያሉትን ሙዚቃዎች)

ማስተሪንግ እና እድሳት (ሪስቶሬሽን)፡ ጆናታን ዴከርስ

ወደ ቴፕ መገልበጥ፡ አንደርስ አፍ ክሊንትበርግ እና ጆናታ ዴከርስ

ምርምሮች፣ፎቶዎች እና ስካኖች፡ ሰላም ወልደማርያም እና አንድምታ ኮሌክቲቭ እና ኦንላይን ማጋዚን

ላይነር ኖትስ፡ ናታን ሀመልበርግ

© & ℗ ሙዚቃዊ 2025 በጆቫኒ ሪኮ እና ሰላም ወልደማርያም ልዩ ፍቃድ የተዘጋጀ

Here goes the artist quote. Here goes the artist quote. Here goes the artist quote. "

Ibex Band

Official Video “Nnnnn”

Choose your preferred music service

Social media links

Press images