ዳዊት ይፍሩ

Dawit Yifru LP fornt cover

ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት የሆነው ሙዚቃዊ ዛሬው እለት የዳዊት ይፍሩን አልበም በድጋሚ አሳትሞ ለገበያ አቅርል።

ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት የሆነው ሙዚቃዊ በዛሬው እለት የኢትዮ-ጃዝ አቀናባሪ የሆነው የዳዊት ይፍሩን በስሙ የተሰየመውን አልበም በድጋሚ አሳትሞ ለገበያ አቅርቧል። ይህ አልበም በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ እጅግ በጣም ጠቃሚ ከሆኑ ዘመናት መካከል አንዱን በድጋሚ እንዲመለከቱ እድሉን የሚሰጥ ነው።

ይህ 11 ሙዚቃዎችን የያዘው አልበም ቀደም ሲል በካሴት የተለቀቁ በመሳሪያ ብቻ ተቀነባብረው በድጋሚ ማስተር የተደረጉ የሙዚቃ ስብስቦችን የያዘ ነው። ሙዚቃዎቹ ከኢትዮጵያ ችክችካ፣ ትዊስት፣ ኮንጎሊዝ ሩምባና ዋልትዝ ሙዚቃዎች ጋር የተዋሃዱ በመሆናቸው በጊዜው በአፍሪካ ቀንድ የነበሩ ልዩ የሙዚቃ አይነቶችን ያሳያሉ። በዚህ አልበም ዳዊት ይፍሩን በጊዜው ከነበሩ የሞያ አጋሮቹ ጥልቅ የሙዚቃ እውቀት የነበረው አቀናባሪ የሚያደርገው ፤ አዲስ በሆነ አቀራረብ የቫዮሊን የሙዚቃ መሳሪያን በሙዚቃ ቅንብሩ ውስጥ ማካተቱ ነው ።

“እነዚህ ነገሮች በጋራ ተዳምረው ይህ አልበም ደማቅ፣ለመንፈስ ምግብ የሚሆንና የሙዚቃ ብዝሃነት ያለው’’ በሆነ መልኩ ፈጥረውታል ይላል የሙዚቃዊ መስራች ተሾመ ወንድሙ። “በዚህ ቅንብር፣ ዳዊት ይፍሩ ጥልቅና ውስብስብ የሆነውን እንዲሁም ግሩም ታሪክ የሚናገረውን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ትዕይንትን ማየት የሚያስችል ብሩህ መስኮት ይከፍታል ፤ እኛም ይህንን ታሪክና ድምጽ ለዓለም የምናደርስ መልዕክተኞች አድርገን እራሳችንን እንቆጥራለን።’’

ይህ ቅንብር የሙዚቃዊ ክምችትና ጥናት ፕሮጀክት የመጀመሪያ ይፋ የሆነ ስራ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ወደ ውጭ አገራት ወጥተው የማያውቁ እጅግ የተወደዱ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎችን በድጋሚ በመቅረጽና በማሳተም፤ ሙዚቃቸው ለዓለም አቀፍ ገበያ ቀርቦ ለማያውቅ ሙዚቀኞች ዝናና እውቅና ለማምጣት ያለመ ነው!

‘’ሁሉም አገራት የየራሳቸው ኮከቦችና የሚወደዱ ድምጻውያን አሏቸው ነገር ግን ከየዘመኑ ነጥረው የሚወጡ ደሞ አሉ፤ ዳዊት ይፍሩም ከነዚህ ጥቂት ነጥረው ከወጡ ሙዚቀኞች ውስጥ አንዱ ነው። በ1970ዎቹ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ኢንዱስትሪ በአዲስ አበባ ብቻ ያበበ የነበረ በመሆኑ ምክንያት በርካቶች የዳዊት ይፍሩን ሙዚቃ ምናልባትም አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል የሚያደምጡት። ይህም የሆነበት ምክንያት እንደ ኬንያና ዩጋንዳ ያሉ ጎረቤት አገራት የሚገኙ ፕሮዲውሰሮች የአገሪቶቹን የሙዚቃ ቅላፄዎች ቀርጸው ቅጂዎቹንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለበርካቶች ይፋ ሲያደርጉ በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሙዚቃ መቅረጫ መሳሪያዎች የነበረ በመሆኑ ይህ ባለመደረጉ ነው።

‘’ስለዚህ የኛ የክምችትና ጥናት ፕሮጀክት እነዚህ ምርጥ የሙዚቃ ስራዎች ህያው ሆነውና እየተደመጡ እንዲቆዩ ዋስትና የሚሰጥ ነው። በአጠቃላይ ይህ ስብስብ እጅግ ግሩም ሲሆን ልትሰሟቸው ከምትችሏቸው እጅግ ያልተበረዙ ከሆኑ ኢትዮጵያዊ አቀናባሪዎች ውስጥ አንዱ በሆኑት ሙዚቀኛ የተሰራ ነው። የዚህ አልበም መውጣት ዓለም ተጨማሪ አስደናቂ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎችንና ባህልን እንዲያውቅ በር እንደሚከፍት ተስፋ እናደርጋለን።’’

ዳዊት ይፍሩ ከተለያዩ ሙዚቀኞች ጋር ለመስራት እንዲሁም ለእድሜ አጋሮቹ ብቻ ሳይሆን ለአዲሱ ትውልድ ሙዚቀኞች የሙዚቃ ክህሎቱን ለማካፈል ካለው ታታሪነት የተነሳ አሁንም ድረስ በኢትዮጵያ ስሙ አይረሴ ከሆኑ ሙዚቀኞች አንዱ ሆኖ ይገኛል።

 

የሚመርጡትን የሙዚቃ አገልግሎት ይምረጡ

Social media links

Press images