ኪሮስ ግርማይ
ኪሮስ ግርማይ በውቅሮ ትግራይ ሲሆን የተወለደው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በከነማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በአጋዚ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል፡፡ ምንም እንኳን ለሙዚቃ ያለውን ፍላጎትና ፍቅር ቤተሰቦቹ ባይደግፉም ኪሮስ በልጅነቱ ለባህላዊ ውዝዋዜ የነበረው ፍቅር ወደ ሙዚቃ ፍቅር ሊለወጥ ችሏል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለም የኪይ ቦርድና የድምጽ ስልጠና ከቅድስተ ማርያም ኮሌጅ ወስዷል፡፡ ከዛም በኋላ ከድምጽ እስከ ሳውንድ ኢንጅነሪንግ ያሉ ስልጠናዎችን ከትግራይ ቱሪዝም ቢሮ፣ ከብሔራዊ ትያትር እንዲሁም ከሰላም ኢትዮጵያ በመውሰድ የቀይ መስቀል የሙዚቃ ባንድን እንዲሁም የትግራይ ባህላዊ ቡድንን ተቀላቅሏል፡፡
ኪሮስ በ2003/2004 ዓ.ም በ104.4 ኤፍ ኤም የሬዲዮ ጣቢያ ላይ በተካሄደ የድምጻውያን ውድድር ላይ በመሳተፍ ምርጥ አስር ውስጥ መግባት ችሏል፡፡
በትግራይ ባህላዊ ቡድን 10 አመታትን ያሳላፈው እንዲሁም የሙሉ ጊዜ ሙዚቀኛ በመሆን በአማርኛ፣ ሱማሊኛ፣ኮንሶ፣አፋርኛና አፋን ኦሮሞ የሚጫወተው ኪሮስ የተለያዩ ኃይማኖታዊ በዓላት እንዲሁም የብሔር ብሔረሰቦች ባሉ የተለያዩ በዓሎች ላይ በመላው ኢትዮጵያ ዝግጅቱን አቅርቧል፡፡ በተጨማሪም በሰርግ፣የሙዚቃ ዝግጅቶች እንዲሁም የምሽት ክለቦች ላይ ስራውን ያቀርባል፡፡ ኪሮስ እንደ ‘ነቀለ ልበይ’ ‘ሱ በል’ እና ‘መርሃባ’ ባሉ እውቅ ዘፈኖቹ ለሙዚቃው ዓለም የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡
ኪሮስ አሁን ናፍቆት የተሰኘውን አዲሱ ነጠላ ዜማውን ያወጣ ሲሆን ሙዚቃው በ2013 ዓ.ም በቀጥታ የተቀረጸና ስለአገር ቤት ናፍቆት የሚያወሳ ነው፡፡