በሻዱ አቤቤና ዓለሙ ደቻሳ

ከኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ የተገኙት በሻዱ አቤቤና ዓለሙ ደቻሳ የተገናኙት ሁለቱም አዘውትረው ይሄዱበት የነበረው ዓለም ገና ስቱዲዮ ሲሆን በስቱዲዮ ቆይታቸው የሰሩት የቅብብሎሽ ስራ የሙዚቃዊን ትኩረት መሳብ ቻለ፡፡ በዚህም የተነሳ ሙዚቃዊ ዜማውን በድጋሚ በቀጥታ ቀረጻ አዘጋጅቶታል፡፡

ሁለቱም አርቲስቶች የሙዚቃ ስራዎቻቸውን በየግላቸው እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን ‘’ሚደግንኬ አዱማ’’ የተሰኘ አዲስ የኦሮምኛ የቅብብሎሽ ዜማ ዓርብ ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም በሁሉም የዲጂታል መተግበሪያዎች ለህዝብ አድርሰዋል፡፡ ዜማው አሁን እምብዛም የማይሰተዋለውን የቅብብሎሽ ዜማን ይዞ የቀረበ እና ውበትን እንዲሁም ተፈጥሮን ስለማድነቅ የሚያቀነቅን ሙዚቃ ነው፡፡

የባሌ ምት ያለው ይህ ዜማ በልዩ ሁኔታ ዘመናዊ ዘይቤን ከባህላዊ ይዘት ጋር ያዋሃደ ነው፡፡ ግጥሙ የተጻፈው በሳሚ ዋቁማና ቤከን ሳርቤሳ ሲሆን ሳሚ ዋቁማ በተጨማሪነት ዜማውን አቀናብሮታል፡፡

ዜማውን እውቁ ሳክስፎኒስትና አቀናባሪ ጆርጋ መስፍን ሪአሬንጅ ማድረጉም አዲስና ማራኪ ይዘት እንዲላበስ አድርጎታል፡፡

 

‘’ሚደግንኬ አዱማ’ የሙዚቃ ቪዲዮ

የሚመርጡትን የሙዚቃ አገልግሎት ይምረጡ

Social media links