የጆርጋ መስፍን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ አልበም ሸክላን ቀድመው ይዘዙ

ሙዚቃዊ ታዋቂውን ሙዚቀኛ ፣ አሬንጀር እንዲሁም ፕሮዲውሰር የሆነውን ጆርጋ መስፍንን ሲያቀርብላችሁ ኩራት ይሰማዋል፡፡

በሙዚቃ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ መፍጠር የቻለው ጆርጋ መስፍን አሁን ደግሞ ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ በተሰኘ አዲስ አልበም ወደ እናንተ መጥቷል፡፡ ‘ ከሁሉ የላቀው ደግ’ በተለይም የኢትዮጵያ ጃዝ ሙዚቃ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ይዘቶች ጋር መንፈሳዊነትን በማዋሃድ ኢትዮ ጃዝን የሚያስቃኝ አልበም ነው፡፡ 

በሙዚቃዊ አማካኝነት ዓርብ ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም በዲጂታል መተግበሪያዎች ሊለቀቅ ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’  አልበም ሸክላን ከታች በተቀመጡት ሊንኮች ማዘዝ ይችላሉ፡፡