የአፀደማርያም ፍቅሬ ‘ብሩህ’ የተሰኘ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ!

‘ብሩህ’ የአፀደማርያም ፍቅሬ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ፡፡ድምጻዊት አፀደማሪያም ፍቅሬና እንደ ጆርጋ መስፍን፣ ተፈሪ አሰፋ፣ ግሩም መዝሙር እና ሄኖክ ተመስገን ያሉ ኮከቦች የተሰባሰቡበት ‘ብሩህ’ የተሰኘ መንፈስን የሚያድስ አዲስ ነጠላ ዜማ ሙዚቃዊ ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እና በዲጂታል መተግበሪያዎች ለህዝብ አደረሰ፡፡ መልዕክቱ ስለአዲስ አመት የሆነው ይህ ሙዚቃ የተለቀቀበት ጊዜ ከአዲስ ዓመት ክብረ-በዓል ጋር የሚገጥም ነው፡፡ 

‘ብሩህ’ የኢትዮጵያ ሙዚቃ  ትሩፋት የሚከብርበት ‘አንቺ ሆዬ ለኔ’ በተሰኘው ባህላዊ ቅኝት ላይ የተመሰረተ ሙዚቃ ነው፡፡ ሙዚቃው እንደ ትሮምቦን እና ትራምፔት ያሉ የሙዚቃ መሳሪያዎች ነፍስ የዘሩበት ሲሆን ይህም በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ የግርማዊ ንጉሰ ነገስት ባንድ ቅላጼን የሚያስታውስ ነው፡፡ በሙዚቃው ላይ ግሩም የትሮምቦን፣ትራምፔት እና ሌሎች የሙዚቃ መሳሪያዎች ከተለያዩ ምቶች ጋር ሆነው በመውጣት በመውረድ ቀልብን የሚገዛና የሚያነቃቃ ድምጽ ይፈጥራሉ፡፡

‘ብሩህ’ ሙዚቃ አንኳር ላይ የአፀደማሪያም ልብ የሚሰርቅ ድምጽ ይገኝበታል፡፡ በውብ ቅላጼውና ጥልቅ ስሜትን በመያዙ የሚታወቀው የአፀደማርያም ድምጽ እንደ አስቴር አወቀ፣ብዙነሽ በቀለ እና ኩኩ ሰብስቤ ያሉ ድምጻውያን ተጽእኖ ያረፈበት ሲሆን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ትሩፋትን የሚያንጸባርቅ ነው፡፡ የድምጿ ዘይቤ አስቴር አወቀን የሚያስታውስ እና እንደ አስቴር አወቀ ስሜትን በዳበረ ሁኔታ የመግለጽ ችሎታን እንዲሁም ግርማ ሞገስን የያዘ ነው፡፡

አፀደማርያም የእነዚህን አንጋፋ አርቲስቶ ስራዎች በምትኖርበት በማድመጥ እና በምትኖባት ባህር ዳር ከተማ በመጫወት ችሎታዋን አዳበረች፡፡ በዛም በአካባቢው ያሉ ክለቦች እንዲሁም በተለያዩ ክብረ-በዓላት ላይ የሚገኙ አድማጮችን ቀልብ ገዛች እራሷም ሙዚቃ ውስጥ ሰጠመች፡፡

አፀደ ማርያም ዓ.ም  በባህር ዳር የተካሄደው ሰላም ፌስቲቫል ላይ ከሙዚቃዊ ጋር ስትገናኝ ነበር በሙዚቃ ህይወቷ ጉልህ ምዕራፍ የተከፈተው፡፡ በዚያን ጊዜ አንጋፋው ሙዚቀኛ መሀሙድ አህመድን ለማጀብ ወደ ባህር ዳር ከተጓዙ ቁንጮ ሙዚቀኞች ጋር ጎን ለጎን ሙዚቃን ለመጫወት እድሉን አገኘች፡፡ ባንዱ እንደ ሄኖክ ተመስገን፣አበጋዙ ሺዖታ፣ግሩም መዝሙር እና ያሬድ ተፈራ ያሉ እውቅ አርቲስቶችን የያዘ ነበር፡፡ አፀደማርያም በዛን ጊዜ ያቀረበችው የመድረክ ላይ ስራ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ባህል ጋር ያላት ቁርኝት የነዚህን እውቅ ድምጻውያን ቀልብ መሳብ ቻለ በተጨማሪም ከሙዚቃዊ ጋር ጥምረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆነ፡፡ 

ብሩህ አዲስ ነጠላ ዜማ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ የካበተ የሙዚቃ ባህል የከበረበት እና እያደገ ያለው የድምጽ መልክዓምድር ማሳያ ነው፡፡          

ወደ ሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም ዲጂታል መተግበሪያዎች በማምራት ሙዚቃውን እንድታደምጡ እንጋብዛለን!