የሙዚቃዊ አርቲስት የሆነውና ከውቧ ይርጋለም ሲዳማ ከተማ የተገኘው አርቲስት ተመስገን ቱማቶ፣ ‘ደስ አለኝ’ የተሰኘ ነጠላ ዜማው ተለቀቀ፡፡
ተመስገን ድምጹ አዘውትሮ ሙዚቃዎቹን የሚጫወተውን አርቲስት መሀሙድ አህመድን እንደሚመስል መድረክ ላይ ሲጫወት ያዩት ተመልካቾች ይናገራሉ፡፡ በቤተክርስቲያን ማኅበረሰብ ውስጥ ተኮትኩቶ ያደገው ተመስገን፣ ህይወት የተሞላበትና ውብ የሆነው ድምጹ ከሌሎች ለየት ብሎ ጎልቶ እንዲታይ ያደርገዋል፡፡ በልጅነቱ በቤተክርስቲያን በዘማሪነት ካበረከተው አስተዋጽኦ አንስቶ ይርጋለም በሚገኘው በቤዛ የወጣቶች ማዕከል እና ሲዳማ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ እስካሳለፈው መልካም ተሞክሮ ድረስ የተመስገን የሙዚቃ ጉዞ በብዙ ሂደቶች ውስጥ ያለፈና ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ነው፡፡
ተመስገን ቱማቶ የ ‘ደስ አለኝ’ ን ግጥም እና ዜማን የደረሰ ሲሆን ይህም ዘርፈ-ብዙ ተሰጥኦ እንዳለው ምስክር ነው፡፡ እንደ ኬኒ አለን እና ጆርጋ መስፍን ያሉ እውቅ ሙዚቀኞች የተሳተፉበት ይህ የሙዚቃ ስራ ስለአንድነትና ስለተስፋ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡
ተመስገን ከመንፈሳዊነትና ከቤተሰብ ያገኛቸውን እሴቶች ‘ደስ አለኝ’ ነጠላ ዜማ ውስጥ ያካተተበት መንገድ ዘፈኑን ባህል፣ስሜት እና የሰው ልጅ መንፈሳዊ ጥንካሬን የማንጸባርቅ ኃይል አላብሶታል፡፡ በሙዚቃዊ የተዘጋጀው የተዋጣለት አሬንጅመንት የሙዚቃው ቅንብር ላይ ነፍስ በመዝራት ለአድማጭ ልብና መንፈስ ተስማመሚ ውህደት ይፈጥራል፡፡
‘ደስ አለኝ’ አሁን በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም በሁሉም ዲጂታል መተግበሪያዎች ላይ ይገኛል፡፡