የስንታየሁ በላይ የ2015 ዓ.ም አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል ሙሉ የመድረክ ስራ ቪዲዮ አሁን ይገኛል!

የስንታየሁ በላይ በላይ የ2015 ዓ.ም አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል ሙሉ የመድረክ ስራ አሁን በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል ላይ ይገኛል! ስንታየሁ ገሚስ አልበሟ ላይ ከሚገኙ ስራዎቿ ከአምስቱ አራቱን መድረክ ላይ በማቅረብ የታዳሚዎችን ትኩረት ስባለች፡፡ 

ከሙዚቃዊ ጋር በመሆን ስንታየሁ ፀደይ የተሰኘ አምስት ዜማዎችን የያዘ ገሚስ አልበሟን ከሁለት አመታት ገደማ በፊት ለህዝብ እንዳደረሰች የሚታወስ ነው፡፡በተጨማሪም ስንታየሁ በቅርቡ ከባልከው ዓለሙ ጋር በመሆን ከሃሳቤና ይገርማል የተሰኙ ሁለት የቅብብሎሽ ዜማዎችን ለህዝብ አድርሳለች፡፡

የአዲስ ጃዝ ፌስቲቫል የመድረክ ላይ ስራዋን ሙዚቃዊ ዩቲዩብ ላይ ተመልከቱ፣አድምጡ፤እንዳያመልጣችሁ!