የሙዚቃ መብት ወኪል

ለዜማ ደራሲዎችና የሙዚቃ ማህደር ውከላ

እንደ ሙዚቃ አሳታሚ ከሙዚቃና ከሙዚቃው በስተጀርባ ካሉ ፈጣሪዎች ጋር በቅርበት እንሰራለን። ዋና ተግባራችን ደግሞ የሙዚቃ ፈጣሪዎችን ገቢ ማሳደግ፣ የዘፈን ደራሲያን መብቶችን ማስጠበቅ እና የፈጠራውን ስራ ሂደት የሚያሳልጡና የሚያቀላጥፉ የድጋፍና እገዛ ተግባራትን እናከናውናለን፡፡

ከነባርና አዳዲስ የዜማ ደራሲያን እና አቀናባሪዎች ጋር አብረን እንሰራለን፡፡ በተለይም የፈጠራ ክህሎታቸውን ለማዳበር የሚያደርጉትን ጥረት በማገዝ፣ በማበረታታት እና በመደገፍ፣ እንዲሁም ለሙዚቃ ስራዎቻቸው የሚያስፈልጋቸውን መገልገያዎችን በማቅረብ እና በመደገፍ አብረናቸው እንሰራለን ። ከዚህ በተጨማሪ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው ነባር የግንኙነት መረቦቻችንን አማካኝነት ሙዚቃን ለንግድ ዓላማ ማዋል ከሚሹ የንግድና የሚዲያ ተቋማት ጋር በማስዋወቅ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እንሰራለን፡፡

እንደ ሙዚቃ አሳታሚ ለደንበኞቻችን የሚከተሉትን አገልግሎቶች አንሰጣለን።