ሙዚቃችንን ለመላው ኢትዮጵያ እና ለአለም ለማዳረስ በጋራ ከምንሰራቸው በርካታ አጋሮች አንዱ ከሆነው የዲጂታል አከፋፋዩ ዘ ኦርቺድ(The Orchard) ጋር አጋርነታችንን ስንገልጽ በደስታ ነው።
እንደ ኢንደስትሪው መሪ አከፋፋይ ፣ አርቲስትና ሌብል አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ፤ ዘ ኦርቺድ በዓለም ዙሪያ ያሉ ዲጂታል እና አካላዊ ቸርቻሪዎችን ይደርሳል። በማርኬቲንግ፣ በማስታወቂያ፣ በማመሳሰል ፈቃድ፣ በቪዲዮ ሞኒታይዜሽን፣ በአፈጻጸም መብት አገልግሎቶች እና በሌሎችም የተካነው ዘ ኦርቺድ ሌብልና አርቲስቶችን በዓለም ዙሪያ ካሉ አድናቂዎቻቸው ጋር እንዲገናኙ ያበረታታል።