ዜና

የሙዚቃ አሳታሚነት ውል ከሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን ጋር 

ከኢትዮጵያዊው ሳክስፎኒስት እና የውዳሴ ኢትዮ ጃዝ ቡድን መስራች ጆርጋ መስፍን ጋር የአርቲስትና ፐብሊሺንግ ውል ስምምነት በመፈራረማችን ደስ ብሎናል።  ጆርጋ በኢትዮጵያና አለም አቀፍ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ላለፉት አመታት አሻራን ያስቀመጠ ሙዚቀኛ ነው። በቀጣይ ግሩም ስራዎችን ይዘን እንቀርባለን። ጠብቁን!

ተጨማሪ ያንብቡ »

የአሳታሚነት ውል ከስንታየሁ በላይ  ጋር

  ደምፀ መረዋዋ የሙዚቃዊ የመጀመሪያ ሴት አርቲስት ማክሰኞ ግንቦት 17 ቀን 2022 ዓ.ም.  ከአስደናቂዋ  ድምፃዊት ስንታየሁ በላይ ጋር አዲስ የሪከርድ ስምምነት መፈራረማችንን ስናበስር በደስታ ነው። በኢንዱስትሪው ውስጥ ማራኪ ድምጽ ካላቸው ሴት ድምፃውያን መካከል አንዷ ትሆናለች ተብሎ ይጠበቃል። የመጀመሪያው ገሚስ አልበሟ በቅርብ ቀን ይለቀቃል!

ተጨማሪ ያንብቡ »

«የኔ ዓለም» ገሚስ አልበም (EP) ተለቀቀ!

በ «ፈልጌ» የሙዚቃ ቪዲዮ የተዋወቃችሁት ባልከው አለሙ «የኔ ዓለም» በተሰኘ ገሚስ አልበም (EP) በድጋሜ ይዘንላችሁ በመምጣታችን ደስታ ተሰምቶናል፡፡ በዚህ ገሚስ አልበም (EP) ዘውዲቱ፣ ለፍቅር ብለን እንዲሁም የትዝታ ፈረስ የተሰኙ ወደር የለሽ ሙዚቃዎች የተካተቱ ሲሆን ግሩም መዝሙር አቀናብሯቸዋል፣ ብዙ እውቅ ሙዚቀኞችም ተሳትፈውባቸዋል፡፡ Youtube Playlist ገሚስ አልበሙን በመረጧቸው የሙዚቃ መተግበሪያዎች ያድምጡ

ተጨማሪ ያንብቡ »

የአሳታሚነት ውል ከአኒስ ገቢ ጋር

በዚህ አመት አስደናቂ የኦሮምኛ ሙዚቃዎች ይደርስዎታል ከድንቁና ባለችሎታው ሙዚቀኛ አኒስ ገቢ ጋር የአሳታሚነት ውል በመፈራረማችን ደስ ብሎናል፡፡ አኒስ አስደናቂ ችሎታ ያለው ወጣት ድምፃዊ ሲሆን በዚህ አመት ስራቸውን ከምንለቃቸው አርቲስቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ የአኒስ ገቢ አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ በቅርቡ ይለቀቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ »

​​ከአስደናቂው አርቲስታችን ባልከው አለሙ ጋር የአሳታሚነት ውል በመፈራረማችን ታላቅ ደስታ

ተሰምቶናል፡፡ ባልከው በዚህ አመት ስራዎቻቸውን ከምንለቃቸው አስራ ስድስት አርቲስቶች መሀከል አንዱ ነው፡፡ባልከው አለሙ በመጪዎቹ ጊዜያት ከታዋቂዎቹ የሙዚቃ ባለሞያዎች አንዱ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ድንቅ ባለተሰጥዖ ሙዚቀኛ ነው። ባልከው ከሙዚቃው ጎን ለጎንም የቅርብ ጓደኞቹ እንደሚመስክሩለት ጎበዝ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ »

ጋዜጣዊ ጥቆማ: የሙዚቃዊ መክፈቻ

የኢትዮጵያን ሙዚቃ ኢንደስትሪ ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚሰራ ድርጅት ተቋቋመ
የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢንደስትሪ ወደ አለም አቀፍ ደረጃ የማሸጋገር ዓላማ ይዞ የተቋቋመው አዲሱን ድርጅታችንን “ሙዚቃዊ”ን እናስተዋውቅዎ፡፡
ድርጅታችን የተቋቋመው በሙዚቃ ኢንዱስትሪው በኢትዮጵያ ካካበተው የ17 አመታት የስራ ልምድና የ25 ዓመታት የዓለምአቀፍ ተሞክሮ መሰረት ሲሆን እ.ኤ.አ በ2022 አስራ ስድሰት ሙዚቀኞችን እና ከመቶ በላይ የሙዚቃ ስራዎች በመላው አለም ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ »

ለአዲሱ የዲጂታል መድረክ፤ “ላይቭና ክሎዝ አፕ” በዝግጅት ላይ

ላይቭና ክሎዝ አፕ በተሰኘው አዲሱ የዲጂታል መድረካችን ተከታታይ ኮንሰርት ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ነን። በእውቁ አርቲስት ጆርጋ መስፍን ፕሮዲውስ የተደረገውና ለረጅም ጊዜ ስናዘጋጅ በከረምነው ሶስተኛው ዙር የላይቭና ክሎዝ አፕ መድረክ የሰባት አርቲስቶችን ሙሉ ስራዎች የምናቀርብ ሲሆን የመጀመሪያ ስራችንን መልቀቅ የምንጀምረው በታዋቂው አርቲስት እሱባለው ይታየው ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ »