እኛ ማነን

የዓለም ማህበረሰብ በብዝሀነትና ህብረቀለማት ያሸበረቀውን የኢትዮጵያን የሙዚቃ ጥበብ ውጤቶችን ልህቀት ማወቅና ማጣጣም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ሊፈጠርለት ይገባል

የዓለም ማህበረሰብ በብዝሀነት ህብረቀለማት ያሸበረቀውን የኢትዮጵያን የሙዚቃ ጥበብ ውጤቶችን ልህቀት ማወቅና ማጣጣም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ አልተፈጠረለትም፡፡

በእኛ በኩል የአገራችን ሙዚቃ አሁን ካለበት የዓይን-አፋርነት ጓዳ ወጥቶ በዓለም አቀፍ የጥበባት መድረኮች ላይ ደምቆ እንዲታይና ተገቢውን እውቅና እና የተጠቃሚነት ድርሻ እንዲኖረው የማድረግ ተልዕኮ ያለውና ሙዚቃዊ ተብሎ የሚጠራ አዲስ ኩባንያ አቋቁመን በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡

ለዚህ ተልዕኮ መሳካት የአጋሮቻችን  ጥረትና ተሳትፎ  ጉልህ ድርሻ ያለው በመሆኑ ከሁሉ አስቀድመን  ኑ አበረን እንስራ  የሚለውን  የአክብሮት  ግብዣችንን  ማቀረብ  እንወዳለን፡፡

ዛሬ ላይ በዚህ መልኩ ግዘፍ ነስቶ እውን ሊሆን የበቃው ሙዚቃዊ መሰረቱ የተጣለው ቀደም ባሉት 17 ዓመታት የአገራችንን ባህልና ሙዚቃ ለማወቅና ለማበልፀግ በሁሉም  የኢትዮጵያ ክልልሎች  እንቅስቃሴ ባደረግንባቸው  ጊዜት ያካበትነው  ልምድ ተጠቃሸ ነው፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ ለ25 አመታት የዘለቀው  የዓለምአቀፉ የሙዚቃ ኢንድስትሪ ተሞክሮዎቻችን  ለሙዚቃዊ እውን መሆን የማይተካ ድርሻ አበርክቷል፡፡

ኩባንያችን የሚያደርገው እንቅስቃሴ በሙዚቃው ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም::  ይልቁንም ሁሉም ያገራችን የፈጠራ ጥበባትና ተዋንያን ተገቢውን እውቅና ተሳትፎና ጥቅም እንዲያገኙ ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን ሁሉ ያከናውናል፡፡ የጥበባቱ ተዋንያን ማለትም  ሙዚቀኞች፣ ዜማ ደራሲዎች፣ አቀናባሪዎች ፣ የስቱዲዮ ሙያተኞች፣  ኤዲተሮች ፣የማስታወቂያ ባለሙያዎች ሁሉ ፍትሃዊ  ተሳትፎና የተጠቃሚነት እድልና ድርሻ  እንዲኖራቸው  ለማድረችን  በትጋት  እንሰራለን ፡፡

ሙዚቃዊ  በአዲሰ አበባና  ስቶክሆልም በሚገኙ ቢሮዎቹ አማካኝነት  ፈርጀ  ብዙ ተግባራትን  ያከናውናል ፡፡  እንደድርጅት የሙዚቃ ህትመትና ቅንብር ፣ የዝግጅትና ስርጭት ፣ የስቱዲዮ አገልግሎት  ይሰጣል፣ በአገር ውስጥና በውጪ የማስተዋወቅና የትስስር ተግባራትን ያከናውናል፡፡  የሙዚቃ፣ የሙዚቃ መሳሪያዎችና  የስቱዲዮ  መገልገያ አቅርቦት ላይ  ይሰራል፣ አርቲስቶችን  የማስተዳደርና የማስተባበር ፣ የፈጠራ ጥረታቸውን  የማገዝና  የመደገፍ  ተግባራትን ሁሉ ያከናውናል፡፡ የሙዚቃ  ኮንሰርቶችንና ሌሎች  ሁነቶችን ያዘጋጃል  ፣ አፈጻጸማቸውን  የመምራትና  የማስተባበር  ተግባራትን  ሁሉ ይከውናል ፡፡

ተልዕኮችን

“ድንቅ የሙዚቃ ጥበብ ውጤቶችን በማፍራት ለዓለም ህብረተሰብ እናደርሳለን፤ የፈጠራ ሙያተኞችን ለማስተባበርና ጥረታቸውን ለማጎልበት በቁርጠኝነት እንሰራለን!“

ራዕያችን

“ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውጤቶች በዓለም ዙሪያ የሚያሰራጭ ተቀዳሚና ተመራጭ ተቋም መሆን ነው ”