አርቲስት ማኔጅመንት

የአርቲስቶች ውክልና አስተዳደርና ስልት

እንደ ሙያተኛ አስተዳዳሪዎች የአርቲስቱን የሙያ ክህሎት ለማሳደግ ብቻ ሳይሆን ሁለንተናዊ እድገቱን ለመቅረጽ በአጭርና እና በረጅም ጊዜ አቅድ አውጥተን በተጠና መንገድ እንሰራለን፡፡ ደንበኞቻችን በተለያዩ የሙዚቃ ስራ ማሳያ መድረኮች ላይ እንዲሳተፉ እናበረታታለን እናግዛለን፡፡ የአልበም ዝግጅትን ማቀድ፣ የአልበም ምረቃና የማስተዋወቅ ስራዎችን፣ ስራውን የሚያስተዋውቁና ተጨማሪ ገቢን ለሙያተኛው የሚያመጡ የተለያዩ ስልቶችን በማመላከት እንዲሁም የረጅም ጊዜ የሙያ ግቦችን እንዲያሳኩ የሙያና የአመራር ድጋፍ እንሰጣለን፡፡ ይሁን እንጂ ተግባሮቻችን ከነዚህ ተግባሮችም በጣሙን የላቁ ናቸው፤ በውል ውስጥ የተስማሙበትን መብትና ጥቅማጥቅሞች ያላገኙ ደንበኞቻችንን በመወከል ለመብታቸው መታገል፣ ደንበኛን ወክሎ ከአዘጋጆች፣ ወኪሎች እና አስተዋዋቂዎች ጋር ለደንበኛ ጥቅም የማግባባት ስራዎችን መስራትና ከዚያም አልፎ ደንበኛን የአእምሮ እና የአካል ጤንነታቸውን ማሻሻል እንዲችሉ ማገዝ ይገኙበታል። በቅርቡም፣ በሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ እየታዩ ላሉ ለውጦች ምላሽ ለመስጠት፤ አስተዳዳሪዎች የሙዚቃ ባንድ ብራንድ ያለውን ዋጋ በአግባቡ በመጠቀም ብዙ ጊዜያቸውን አዳዲስ የገቢ ምንጮችን እና ስልታዊ አጋርነቶችን በመፍጠር ላይ ያውላሉ።