ለአዲሱ የዲጂታል መድረክ፤ “ላይቭና ክሎዝ አፕ” በዝግጅት ላይ

ላይቭና ክሎዝ አፕ በተሰኘው አዲሱ የዲጂታል መድረካችን ተከታታይ ኮንሰርት ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ነን።

በእውቁ አርቲስት ጆርጋ መስፍን ፕሮዲውስ የተደረገውና ለረጅም ጊዜ ስናዘጋጅ በከረምነው ሶስተኛው ዙር የላይቭና ክሎዝ አፕ መድረክ የሰባት አርቲስቶችን ሙሉ ስራዎች የምናቀርብ ሲሆን የመጀመሪያ ስራችንን መልቀቅ የምንጀምረው በታዋቂው አርቲስት እሱባለው ይታየው ነው፡፡